አጠቃላይ የሆሳዕና ከተማ ዳራ ነባራዊ ሁኔታ

የሆሳዕና ከተማ ስያሜን በተመለከተ

የሆሳዕና ከተማ በደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከሚገኙ ከተሞች መሀል አንዷ ሰትሆን ከአዲስ አበባ በሰተ ደቡብ በ230 ኪ.ሜ እና ከሀዋሳ በሰተ ሰሜን ምዕራብ በ168ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ የሀዲያ ዞን ርዕሰ-ከተማ ናት፡፡

ከተማዋ ዛሬ የምትጠራበትን ስያሜ (ሆሳዕና)የሚለዉን ከማግኘቷ በፊት ዋቸሞ በመባል እንደምትታወቅ የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ሆሳዕና የሚለዉ ስያሜ የተሰጣት በአፄ ሚኒልክ ዘመን ራስ አባተ ቧያለዉ በ1888 ዓ/ም የአዉራጃ ነዢ በመሆን ወዚች ከተማ ሲገቡ ዕለቱ የፋስካ (የትንሳኤ) በዓል ሊከበር አንድ ሳምንት ሲቀረዉ ወይም የትንሳኤ በዓል ከሚከበርበት እሁድ ቀደም ብሎ ባለዉ ሳምንት  እሁድ ቀን ነበር ፡፡ዕለቱ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሆሳዕና በመባል ይታወቃል፡፡  በዕለቱ በአከባቢዉ የነበረዉን ሰላምና ያገኙትን ዕረፍት በማሰተዋል ገዢዉ ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም ስያሜዋን ሆሳዕና ብለዉ እንጠሯት ከሚነገሩ አፈ ታሪኮች መረዳት ተችሏል፡፡ በመሠረቱ ሆሳዕና የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ሲሆን ትርጓሚዉም “በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ’ አሁን አድን ማለት ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ የአካባቢዉ ሕብረተሰብ ሁለቱንም  ስያሜዎች (ዋቸሞንና ሆሳዕናን)በአቻነት የሚጠቀም ቢሆንም በዋናነት የከተማዋ ስያሜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በይበልጥ የሚትታወቀዉ ሆሳዕና በሚለዉ መጠረያዋ ነዉ፡፡

ዋቸሞ የሚለዉ ቃል ሀድይሳ(የሀድያ ቋንቋ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም መምነሸነሸ፣ሁሉም ነገር ሙሉ፤መንፈላሰሰ፤በጥሬ ትርጉሙ ሲታይ ደግሞ ምቾትን፣ፀጋን፣ተድላን፣ ዉበትንና ማራኪ የተፈጥሮ ገጽታን የሚገልጽ ነዉ፡፡ይኸዉ ስያሜም በከተማዋ ለተለያዩ ተቋማት መጠሪያ ሲሆን ለአብነትም የዋቸሞ ዩቨርሲቲ፣ዋቸሞ መሰናዶና ዋቸሞ ንግድ ባንክ…. ወዘተ በማለት ሰይመዉ እየጠቀሙበት እንደሆነ ማሳያ ነዉ፡፡

The administrative area of Hossana town is 10,414.3 hectares, out of this 4,585.48 hectares of the town has been master planned (Hossana Town Finance and Economic Development Office, 2018)