Enterprise Office
Enterprise Office
Mission
ተልዕኮ/Mission/
ምቹ የሆነ የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት እንዲኖር የድጋፍ ማዕቀፎችን በማጠናከር የኢንዱስትሪዉ ባለቤት የሚሆኑ የግል ባለሀብቱንና ኢንተርፕርነሩን ወደ ዘርፉ በማምጣት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን እንዲሁም አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዉን በማስፋፋት፣ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገዉን መዋቅራዊ ሽግግር በማፋጠን፣ የምርት ጥራትና ምርታማነትን በማሳደግ የሀገር ዉስጥና የኤክስፖርት ገበያ ልማትና ትስስር ስራዎችን በማፋጠን ኢንዱስትሪዉ የመሪነት ሚና እንዲኖረዉ ማድረግ፣ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር፣ የከተማዉን ህብረተሰብን ገቢ ማሳደግና የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት፡፡
Vision
ራዕይ/Vision
በ2017 ዓ/ም በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ የአምራች ኢንዱስትሪ ተፈጥሮ እና በከተማችን የህብረተሰቡ የኢኮኖሚ ዕድገት ደረጃ ተሸሽሎና ተረጋግጦ ማየት ነዉ፡፡
Core Values
መሰረታዊ ዕሴቶችና እምነቶች/Values & operational philosophies/
- ሥራዎቻችን የጋራ አመለካከትን ከመፍጠር ይጀምራሉ!
- በዕቅድ እንመራለን፣
- ፍትሃዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው፣
- በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን!
- ጊዜ እና የሰው ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶቻችን ናቸው፣
- ኪራይ ሰብሳቢነትን እንፀየፋለን፣
- መረጃን ለልማት እናውላለን፣
- ውጤት ያሸልማል፣
- ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!
- ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው!
- የሴቶችን ፣የወጣቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ሁሉአቀፍ ተሳትፎ እናረጋግጣለን!
ዓላማ/Goal/
- የኢንዱስትሪ ልማት ምርታማነት፣ ጥራትንና ተወዳዳሪነትን ማረጋገጥ፣ የማኑፋክቸርንግ ኢንዱስትሪው መሠረቱን በማስፋት በሂደት የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ መሠረት እንዲጥል በማድረግ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ከኢንዱስትሪና ግብርና ጋር በማስተሳሰር የክልሉ ህዝቦች ብልፅግናን ማረጋገጥ፤
- የስራ ፈጠራ ክህሎትና የስራ ፈጣሪነት አመለካከትን በማጎልበት፣ በከተሞች ሰፊ የስራ አማራጮችን በመፍጠርና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ለኢንዱስትሪ መሰረት የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች በማፍራት ስራ አጥነትን በመቀነስ ለሀገራችን ብልፅና ዘርፉ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ማድረግ ነው፡፡