Hosanna city Finance Office
Hosanna City Finance Office
Mission
የተቋሙ ተልዕኮ
በቁጠባ ላይ የተመሰረተ የሀብት አጠቃቀም እንዲሰፍን የተቋሙን አቅም ግንባታ በማከናወን ዘመናዊ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት፣ የፊስካል ፖሊሲ፣ሲቪክና ትብብር ሀብት በማስተባበርና በመምራት፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በማስተባበር፣ አሰራሩን የጠበቀ ግዥ ሥራዓት በመዘርጋት እና የንብረት ማስወገድ ሥራዎችን በማካሄድ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አኳን በዞኑ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ፍትሃዊ ሀብት አሰተዳደር ተግባራዊ እንዲሆን ማስቻል፣
Vision
የተቋሙ ራዕይ
በ2022 የሀገራችን የነፍስ ወከፍ ገቢ 2,220 ዶላር ለማድረስ የተያዘዉን ግብ በዞናችን ለማሳካት የዞኑን ሀብት በብቃት በማሰተዳደር የዜጎችቁሳዊፍላጎት፣ እኩልየልማትተሳታፊነት፣ፍትሃዊተጠቃሚነት እናነፃነትን በማረጋገጥ በሁሉም መስክ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለዉጥ መጥቶማየት፣ በዞናችን ፐብሊክ ሰርቪሱ ዉስጥ በልህቀቱና በውጤቱ መሪ ተቋም መሆን፤
Core Values
የተቋሙ ዕሴቶች /Values/
- የሕዝብ አገልጋይነት፣
- ዉጤታማነት፣
- የስራ ትጋትና ቁርጠኝነት፣
- ህጋዊነት፣
- የሙያ ልቀት፣
- የመማሪና የለውጥ ተነሳሽነት፣
- ተጋግዞ በቡድን መሥራት፤
- የበለፀገ ኢኮኖሚ መገንባት፣
ግቦች/Goals/
- ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ፡፡
- የዞኑን መንግስት የወጪ ፍላጎት ለማጣጣም በዞኑ የሚሰበሰበዉን የገቢ መጠን ማሳደግ፣
- የመንግሥት ጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና ክፍያዎችን ወቅታዊ፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ የተገልጋይን እርካታ ማሳደግ፣
- የሂሳብና ሪፖርት ሥራን በማሻሻል ወቅታዊ፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማረጋገጥ
- የሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ውጤታማነት በማረጋገጥ የተገልጋይ አመኔታ ማሳደግ