Hossain City Administration Planning And Development Office

Mission

ተልዕኮ(Mission)

በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ በመዘርጋት፣ የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው  ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡


Vision

ራዕይ(Vison)

ፍትሃዊ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የክልሉ ሕዝብ ከድህነት ተላቆ “ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት” ሀገራዊ ራዕይ ተሳክቶ ማየት፡፡


Core Values

እሴቶች(Values)

  • ቆጣቢነት
  • ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ
  • ፍትሃዊነት
  • ውጤታማነት
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት
  • ተቆርቋሪነት
  • ቀልጣፋ አገልገሎት
  • በዕቅድ መመራት
  • ሕጋዊነት

 

የተቋሙ ዋና ዋና ዓላማዎች(Goals)፡- የከተማዉን አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታዎችን በማጥናት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማመላከት" ከተማዉ የተገኘውን ሀብት በዕቅድ በመምራትና አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ሥርዓትን ማስፈን የሚያስችል የሀብት ማከፋፈያ ቀመር ማዘጋጀት፣ በከተማ አስተዳደር ሲር ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች በጀት ማዘጋጀት፣ የልማት እቅድና ፖሊሲ አፈፃጸም ጥናትና ትንተና ማካሄድ፣ በከተማዉ ተግባራዊ የሚደረጉ የካፒታል ፕሮጀክቶች የተጣለባቸውን ግቦች በማስካት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ" የከተማዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን ጥራቱን በጠበቀና በአስተማማኝ ሁኔታ በማዘጋጀት ለውሳኔ ሰጪ አካላት"ለፖሊሲ አውጪዎች" ለጥናትና ምርምር ለሚፈልጉ አካላት መረጃ መስጠትና ሁሉኑም መረጃዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አውቶሜት በማድረግ ተደራሽ እንዲሆን ማስቻል፣ የከተማዉን የህዝብ እድገት ምጣኔ ከከተማዉ ኢኮኖሚ የዕድገት ምጣኔ ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ በሥነ-ህዝብና ልማት ዙሪያ ለማህበረሰቡ ሰፊ የትምህርትና ቅስቀሳ ስራዎችን በመተግበር የከተማዉን ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነትና ዘላቂነት እንዲኖረው ማረጋገጥ መሠረታዊ ዓላማዎች ናቸዉ፡፡

Our Location