• Date: Mar 13 2022
  • Office: Hosanna City Culture and Tourism Office
  • Content

    ያሆዴ መስቀላ የሃዲያ ህዝብ ታላቅ ባህላዊ የአዲስ አመት ክብረ በአል ነው እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም

    ወር ሙሉ የሚከበረዉ ያሆዴ መስቀላ አንዷን ቀን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የመስቀል ቀን ጋር መጋራቱ የመገጣጠም ጉዳይ ነው።

    የያሆዴ መስቀላን በዓል ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት በሆነው የክርስቶስ መስቀል ግኝት ጋር የማያያዙ ዝንባሌ ኢትዮጲያ ውስጥ በስፋት ይስተዋላል፡፡ ይህ በሀዲያ እና በሌሎች የደቡብ ክፍሎች ውስጥ በታላቅ ደስታ የሚከበረውና ወር የሚዘልቀውን የአዲስ ዘመን መግቢያ ሥነ-ስርዓት ከእየሱስ ክርስቶስ መስቀል ግኝት ጋር ማያያዝ ፈፅሞ የተሳሳተ አረዳድ ነው፡፡

    ይህ ማለት ግን ይሄን አፈ-ታሪክ የፈጠረችው ቤተ ክርስቲያን ናት ማለት አይደለም፡፡ በሀገር ደረጃ በሀዲያ እና ሌሎች የደቡብ ክልል ማህበረሰቦች ታሪክ ፣ ባህል ፣ እና ዕሴቶች ዕውቀት ማነስ ጋር ተያይዞ እየደረሱ ያሉትን የታሪክ መጣረሶችን መለየት አለብን፡፡ ባህላቸውም ሆነ ታሪኮቻቸው እየተገለለ መምጣቱም ቢሆን ብዙም የማያስደንቅ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡

    በዚህ መልኩ መተርጎሙ ለቤ/ክ አግባብነት ያለው ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን በዓሉ ለሀዲያ ሕዝብ ካለው ትርጉም አንፃር በዚያ መልኩ ማዋሃዱ ተገቢ ያልሆነ ነው፡፡ ይህ ማለት ታሪክን እንደገና መፃፍ እንደማለት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ለሕዝቡ ሌላ የሌለ ታሪክ ከመፍጠር ጋር ሁሉ ሊስተካከል ይችላል፡፡

    በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፣ በፕሮቴስታንቱም ሆነ በካቶሊክ እምነት ተከታይ የሀዲያ ሕዝብ ዘንድ እነዚህን ሁለቱን በዓላት በጣምራ ማክበሩ ቅሬታ ፈጥሮበት አያውቅም ምክንያቱም ሁለቱም በዓላት በታሪክም ሆነ በባህል የተለያዩ ዕሴቶች መሆናቸውንና የቀናቱም መገጣጠም የአጋጣሚ ነገር መሆኑን በሚገባ ተገንዝቦታልና፡፡

    በኢትዮጲያ በበላይነት ተንሰራፎ የሚገኘው ባህል የያሆዴ መስቀላ ባህላዊ ፋይዳውን በመተው በዓሉን በሀይማኖታዊ በዓልነት በመፈረጅ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ጥንታዊ ቅርሶቻቸውንና ባህላቻውን እንዳያስጠብቁ አድርጓል፡፡ በመስቀል በዓል ዕለትም ኢቲቪ ፣ ዋልታ ፣ ፋና እና ሌሎች ማሰራጫዎችም ስርጭታቸውን ‹‹ለክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ›› በማለት ነበር የከፈቱት፡፡ ከህዝቡ በሚሰበሰበው ታክስ በሚተዳደሩ ሚዲያዎች ላይ እንዲህ አይነቱ ስርጭት መተላለፉ የሀዲያን ማህበረሰብ እጅግ ያስቆጣል፡፡

    ለዘመናት በተደጋጋሚ ሲሰራጩ በነበሩ በእነዚህ እና በሌሎች የታሪክ መበረዞች ምክንያት አንዳንድ የሀዲያ ሙስሊም ማህበረሰብ ራሳቸውን ከዚህ ታላቅ ዘመን መለወጫ በዓል ሲያገሉ ተስተውለዋል፡፡ ይህ መገለል በሀገር ደረጃም እየተስተዋለ መሆኑን ተገንዝቤያለው፡፡

    ያደግኩት በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ቤተሰብ ነው፡፡ እኔ የሁለት አመት ሕፃን በነበርኩበት ወቅት ነበር ቤተሰቦቼ ከእስልምና ወደ ፕሮቴስታንት እምነት የተቀየሩት፡፡ አብዛኛዎቹ የዘር ሀረጎቼ እስካሁንም ድረስ የእስልምና እምነትን በመከተል ላይ ናቸው፡፡ ከሁለቱም ቤተ እምነት ተከታዮች ጋር የቅርብ ግኑኝነት ስለነበረኝ በሁለቱም የሀይማኖት ጎራዎች ስላሉ ልምምዶች እንግዳ አይደለሁም፡፡

    ያሆዴ መስቀላ ለክርስቲያኑ ቤተሰቦቼ የተቀደሰ በዓል እንደመሆኑ ሁሉ ለሙስሊሙ ቤተሰቦቼም እንደዛው ነበር፡፡ ሊመሰገን በሚገባ መልኩ እስካሁን ድረስ በሁለቱም ቤተሰቦቼ ዘንድ በተለየ ድምቀት ይከበራል፡፡ ከክርስትና እምነት ጋር ብቻ መያያዙ በሌሎች የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ለበዓሉ ያለው ክብር ሊሻር ይችላል የምል ስጋት አለኝ፡፡

    የተሳሳተ ትርጓሜ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤቶቸ

    • ከለምንም ታሪካዊ መሰረት ያሆዴ መስቀላን ሃይማኖታዊ በማድረግ የሀዲያ፣ የደቡብን ብሎም የመላው ኢትዮጲያ ሙስሊሞችን ከበዓሉ ያገላል፡፡ ይህ ተግባር አያቶቻቸውና ቅድመ አያቶቻቸው ለዘመናት ካከበሩትና ከተደሰቱበት በዓል ሙስሊሞ ልጆቻቸዉን ማግለል እንደማለት ነው፡፡
    • ለመጪው ትውልድ የተዛባን ታሪክ ማውረስሞ ይሆንብናል ፡፡
    • የህዝብን ባህል ፣ ልማድ እንዲሁም የኑሮ ዘይቤን ማንኳሰስ ይሆንብናል፡፡ ያሆዴ መስቀላ ለሀዲያ ከማንነቱ ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው፡፡
    • ጎልቶ የሰፋነዉ ባህል የተጎዳ ባህል ያላቸዉ ብሄሮችን የባህል እሴቶች እንደመናድ ነዉ

    የ‹‹ያሆዴ መስቀላ›› እና ‹‹መስቀል›› ልዩነት ማስረጃዎች

    What are the evidence that Yahoode Masqala, most sacred of annual celebrations, is not the same as Mesqel observed by Christians around the same time of the year? Here are a few:

    • ኦርቶዶክስ ሀይማኖት በሀዲያ እና በአብዛኞቹ የደቡብ ማህበረሰቦች ውስጥ ታሪክ ያለዉ እንኳን ቢሆን የአብላጫነት ያለዉ ሀይማኖት ሆኖ አያውቅም፡፡ ማህበረሰቡ ዘንድ አንድም ቀን የአብላጫ ሀይማኖት ሆኖ ከማያውቀው ሀይማኖት በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ክብር ያለው ያሆዴ መስቀላ በዓል ሊወለድ አይችልም
    • ያሆዴ መስቀላ ማንኛቸዉም የክርስትና ተፅዕኖዎች ወደ ሀዲያ ከመምጣታቸዉ በፊት የኖረ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ክርስትና ታሪክ በደቡብ ኢትዮጲያ ከያሆዴ መስቀላ ጋር ሲነፃፀር ውስን ነው፡፡ የፕሮቴስታንት እምነት ደግሞ እጅግ በጣም ውስን ነው፡፡
    • ያሆዴ መስቀላ ለሀዲያ እና ለሌሎች የደቡብ ማህበረሰቦች የአዲስ ዓመት መግቢያ (መጀመሪያ) ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይህ ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አብላጫ በሆኑባቸዉ አከባቢዎች እንኳን አይታሰብም፡፡
    • በሀዲያ ማህበረሰቡ ዘንድ ከበዓሎች ሁሉ የበላይና ትልቅ ክብር ያለው ያሆዴ መስቀላ ሲሆን ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ግን የኢየሱስ ትንሳኤ (ፋሲካ) ነው። ያሆዴ መስቀላ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት መሰረት ቢኖረዉ ይህ ሊሆን አይችልም
    • ያሆዴ መስቀላ በእስልምናም ሆነ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላለፉት ብዙ ትውልዶች በአንድነት ማክበራቸው ይህ በዓል በሀዲያም ሆነ በሌሎች የደቡብ ማህበረሰቦች ዘንድ ከየትኛውም ሀይማኖት ጋር ግኑኝት የሌለው መሆኑን የመላክታል። ከክርስትና ጋር ማጣመር የዛሬ ክስተት ነዉ

    በእነዚህ ምክንያቶች ጋዜጠኞች ድንቁርናን ከማሰራጨት ይልቅ ሰዎችን ለማስተማር እና ለመማር ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡ አንትሮፖሎጂስቶች፣ የታሪክ ምሁራን እና ሌሎች ተመራማሪዎች ይህንን ጨምሮ በኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ አፈ፡ታሪኮችን ማረም መጀመር አለባቸው፡፡ በጌጥ ካሸበረቁ ቢሮዎች ወጥተው በታዋቂ የብዙኃን መገናኛዎች የእነዚህ በዓላትን እውነተኛ አመጣጥ ለህዝቡ ማስተማር ይገባቸዋል፡፡ የሀዲያ ህዝብ እና ሌሎች የደቡብ ህዝቦች እነዚህን እየተዛቡ ያሉትን የታሪክ ዕሴቶቻቸውን ለመጠበቅ መታገል መጀመር አለባቸው፡፡ ይህን የማድረግ ልዩ ግዴታ አለባቸው፡፡

    ምንጭ  https://hadiyajourney.com

  • Date: Mar 24 2022
  • Office: Government Communication Affairs Office
  • Content Ambulance

    በሀዲያ ዞንና በሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች የተደረገው የህዝብ ውይይት መድረክ ፍፁም ጤናማና ሰለማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቆል።

    በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም አካባቢዎች በዛሬው እለት የሚከሄደው የከተማ ነዋሪዎች የውይይት መድረክ በሀዲያ ሆሳዕና ከተማ ፍፁም ሰለማዊ መንገድ ተጠናቆል።

    መድረኩ ለይ አንዳንድ አፍረሽ ሀይሎች ውይይቱን ለማደናቀፍ ቢሞክሩም ውይይቱ የለ ምንም የፀጥታ ችግርና ፍፁም ሰለማዊ በሆነ መንገድና ህብረተሰቡን አሰተፍ በሆነ መልኩ ተጠናቆል።

    በመድረኩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አቶ አብርሃም ማርሻሎ የሲዳማ ብልጽግና ጽ/ቤት ሃላፊና አቶ አሪፍ መሀመድ የሀረሪ ብልጽግና ጽ/ቤት ሃላፊ ተገኝተዋል።

    የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ ሎምቢሶ እና የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ አብርሃም መጫም በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተዋል።

    የመድረኩ ዋና አላማ የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን ለህዝብ ለማስተዋወቅና የከተማውን ህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ለይቶ በጋራ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንደሆነ አቶ አብርሃም ማርሻሎ አስረድተው በብዙ ፈተናዎች መሐል ሆናቹ የዞኑና ከተማውን ማህበረሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለይ ለደረገቹት ታጋድሎ የዞኑን መንግሥት እና ከተማ አስተዳደሩን አመስግናዋሉ አቶ አብራሃም ማርሻሎ።

  • Date: Sep 28 2022
  • Office: Hadiya zone Government Communication Affaris Department
  • Content የያሆዴ መስቃላ በሚድያዎች የማስተዋወቂያ የጊዜ ሰለዳ