Labor And Social Affairs Office

Mission

  •  የሥራ ስምሪት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የኢንዱስትሪ ሠላም እንዲሰፍን፣ የሠራተኛው ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የሥራ አካባቢዎች እንዲሻሻሉና  የዜጐች ማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት (የአካል ጉዳተኞች ዕኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ፣ አረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙና ተሳትፎአቸው እንዲጐለብት፣ በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በድህነት፣ ተጋላጭነትና መገለል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎች) እንዲያገኙ ማድረግ የሚሉት የሴክተሩ ተልዕኮዎች ሲሆኑ
  • በከተማችን፡- ጤናማ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት እንዲዳብር የሠራተኞች ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅ የሥራ አካባቢ እንዲጎለብትና የሥራ ሥምሪት እንዲሰፈን ማድረግ
  • የሕብረተሰቡ በተለይም የቤተሰብ፣የአካል ጉዳተኞች፣የአረጋዊያንና የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ውስጥ የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎችን የማህበራዊ ችግሮችን መከላከል፣ የማህበራዊ ደህንነት ልማትና የተሀድሶ አገልግሎቶችን ማስፋፋት፡፡

 


Vision

  በ2017 የኢንዱስትሪ ሠላም ያሰፈነ፣የሥራ ዕድሎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የማኀበራዊ ደኀንነት ልማትን ያጐለበተ ሞዴል ሴክተር ሆኖ ማየት  


Core Values

 

  • ለለውጥ ዝግጁነት፤ግልጸኝነትና ተጠያቅነት፤አሳታፊነት
  • ውጤታማነት፤የላቀ አግልግሎት፤ፍትሃዊነት፤
  • ለኢንዱስትሪ ሰላም መስፈን በትጋት መስራት፣
  • ማህበራዊ ደህንነትን ማስጠበቅ፣
  • በማህበራዊ ኑሮ ጠንቅ የተጠቁ የህ/ሰብ ክፍሎችን መልሶ ማቋቋምና መደገፍ፣
  • የትብብር የጋራ መግባባት የተቀናጀ አሠራር እና የአሳታፊነት መርህ
  • ፈጣን ምለሽና ቅን አገልግሎት በመስጠት የአገልጋይነት ስሜት መላበስና የተገልጋዮቻችን እርካታ ማምጣት፤
  • የማህበረሰብ አቀፍ ልማት ሥራዎችን አጠናክረን መሥራት፣

 

 (Goals)

  • የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን በማሻሻል የኢንዱስትሪ ሠላም ማስፈን፣
  • የሥራ ገበያ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ከሰው ኃይል ፍላጎትና አቅርቦት ጋር በማስተሳሰርና ተደራሽ በማድረግ የሥራ ሥምሪት ማስፋፋት፣
  • በማህበራዊ ችግሮች የተጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎችን የልማት ተጠቃሚነት በመጨመር ማህበራዊ ችግሮችን መቀነስና መልሶ መቋቋም፣
  • የአካል ጉዳተኞችንና የአረጋውያንን የልማት ተጠቃሚነት በማሻሻል ምርትና ምርታማነትን ማሰደግ፣

 

 

Our Location