09
Aug
2022
የሆ/ከ/አስ/መ/ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነሐሴ3/2014ዓ.ም
በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት አማካኝነት እየተመራ የሚገኘው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአሥራ አራት በተለዩ የስምሪት መስኮች ላይ እየተተገበረ እንደሚገኝ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ታደሰ ገልፀዋል ።
በተለይም በሄጦ ቀበሌ አስተዳደር በወጣቶች አደረጃጀት አማካኝነት በዓለሙ ወ/ሃና ት/ቤት የክረምት ማጠናከርያ ትምህርት ለተማሪዎች በነፃ በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አማካኝነት እየተሠጠ ያለዉ ተግባር መቀጠል ያለበት መሆኑንም ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ዘመድኩን እና የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር አበበ ሎላሞ በበኩላቸው ይህ ተግባር በቀጣይነት በሌሎች ት/ቤቶች ላይ በትኩረት የሚሰራ እና አስፈላጊዉም ትብብር እንደሚደረግላቸው በመግለፅ ለወጣቶቹ ያላቸዉን ምስጋና ገልጸዋል !!!