"ያሆዴ" የሀዲያ ዘመን መለወጫ በዓል በምዕራብ ሶሮ ወረዳ ጃቾ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ስነ-ስርዓቶች ተከበረ

በበዓሉ አከባበር ላይ የባህል ሽማግሌዎች፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች፣የአካባቢዉ ተወላጆች፣ ጥሪ የተደሰገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

መስከረም 12/01/2015ዓ.ም( የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

በፕሮግራሙ መክፈቻ የባህል ሽማግሌዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ፕሮግራሙን በምርቃት ከፍቷዋሉ፥

ያሆዴ በዓልን ምክንያት በማድረግ የወረዳው ም/አስ/ር እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተርኩ ታምረት ባስተላለፉት መልዕክት እንኳን ለሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለልጆች ለአባቶች ለእናቶች የራሳቸው ድርሻ ያለ መሆኑን በማስገንዘብ ከቅድማ ዝግጅት ጀምሮ እስከ መባቻ ድረስ ያለውን ይህንን በዓል ለአለም ህዝብ ለማስተዋወቅና በዓለም በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ ጥረት በመደረግ ላይ የለ ስለሆነ ሁለችንም በዓሉን በአዲስ መንፈስና በመልካም ምኞት ልናከብረዉ ይገባል ብለዋል።

የምዕ/ሶ/ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኤፍሬም ዘነበ እንኳን ለሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት ቀዳም ሲል በተለየዩ ችግሮች እንድሁ በህብረት ለመክበር ባይቻልም በዘንድሮው አመት በተለያ መልኩ ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ ሲከበር ተላቅ ደስታ ይሰማናል ሲሉ የያሆዴ በዓል የተለያ ትርጉምና መገለጫ ለሀዲያ የለ እንደሆነ ገልጸው

በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ሀዲይ ነፈራ ዕለተ ቅዳሜ 14/01/2015 ዓ.ም የበዓሉ ማጠቃለያ በድምቀት ስለሚከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በፕሮግራሙ እንድተዳሚም መልዕክታቸውን አስቀምጧሉ።

በስተመጨረሻም በባህል ሽማግሌዎች የችቧ ማቀጣጠያ ስነስርዓት በማድረግ በዓሉ በሰላም እንድጠነቀቅ በቡራኬና በመደምደሚያው ምርቃት ፕሮግራሙ ተጠናቅቋል ።

ምንጭ:- የወረዳው ኮሙኒኬሽን

Share this Post