የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት 03/2015 ዓ.ም
የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት ስንታየሁ አለማየሁ እንደገለፀው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከመኖሪያ ሰፈራቸው ተፈናቅለው በከተማው በስፖርት ሆቴል ቅጥር ግቢ በጊዜያዊ መጠለያ ከሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች መካከል ማህበሩ 90 ለሚሆኑ ሴቶችና ህፃናት የዳይፐርና የሞዴስ ድጋፍ አድርጓል ።
ድጋፋ ከተፈናቃዮች ቁጥር አንፃር በቂ ባይሆንም የወገን ደራሽ ወገን መሆኑን በመገዘብ ሁሉም የከተማችን ነዋሪ ፈጥኖ ሊደርስላቸው እንደሚገባም አሳስቧል ።
አንዳንድ ድጋፍ የተደረገላቸው ተፈናቃዮች በበኩላቸው ከመስከረም 12/2015ዓ.ም ጀምሮ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ባደረሰባቸው ጥቃት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም ጉዳት ያደረሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል
በህይወት ተርፈው የተሰደዱት በሀድያ ዞን አስተዳደር ድጋፍ በጊዜያዊ መጠለያ እንደሚገኙ በመግለጽ የወገን ድጋፍ እንዳይለያቸው ጥሪ አቅርበዋል ። ይህንን ተግባር ለካናወኑ ለማህበሩ አባላት ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት አሸባሪዎች ተባብረው በከፈቱብን ጦርነት ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉና ጉዳት የሚደርስባቸው አብዛኞቹ ሴቶችና ህፃናት መሆናቸውን ጠቁመው የሀገር ሉአላዊነት ከማስከበር ጎን ለጎን የተጎዱ ወገኖቻችን ለማቋቋም ሁሉም ዜጋ የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል ።