09
Aug
2022
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኒዎሎጂ ጽ/ቤት ለግንባር ቀደም ሠራተኞች የሽልማትናየዕውቅና ፕሮግራም አካሄደ ። የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሐምሌ 28/2014ዓ.ም የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኤርሲኖ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት ዓላው ግንባር ቀደም ሠራተኞችን ለማበረታታት ሲሆን ለሠራተኞቹ እንደ አፈፃፀም ቅደም ተከተላቸው የገንዘብና የቁሳቁስ ሽልማት ተሰጥቷል ። በፕሮግራሙ ላይ የከተማው አፈ-ጉባዔዎችና ቋሚ ኮሚቴዎች ፣የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊዎች ና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ። በሽልማቱ 1ኛ የወጡት አቶ ሠለሞን ጋቦሬ እና 2ኛ የወጡት አቶ ዘለቀ ሃንዲሶ በሰጡት አሰተያየት ሽልማቱ በቀጣይ ይበልጥ ለመስራት የሚያነሳሳቸው መሆኑን በመግለፅ ጽ/ቤቱና ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት አመስግነዋል ።.