በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አስተዳደራዊ ወጪዎችን በመቀነስ ለማህበረሰቡ እሴት ለሚጨምሩ ተግባራት ቅድሚያ በመስጠት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ገለጸ
በሀዲያ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 3መቶ 73 ሚሊዮን ብር ለካፒታል ፕሮጀክቶች በመመደብ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ተገልጿል።
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደለለኝ ሻንቆ እንዳሉት፥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለሀገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ተተኪዎችን ማፍራት የሚያስችል የትምህርት ተቋም እና የመንግስት የቢሮ ክራይ ወጪን በማስቀረት ለልማት ማስቻል ያለመ ተግባር ተከናውኗል።
የኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ማስታወሻ ሀውልት ግንባታ በዞኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በካፒታል ፕሮጀክት ተይዘው ተግባራዊ ከተደረጉ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ሲሆን ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በሆሳዕና ከተማ በስሙ በተሰየመው አደባባይ ላይ የማስታወሻ ሀውልቱ እንዲገነባ ተደርጓል።
ባለ 6 ወለል የዞኑ አስተዳደርና የሴክተር መስሪያ ቤት የጋራ ህንጻ እና የሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ማጠናቀቂያ ስራዎች እንዲሁ በዓመቱ በካፒታል ፕሮጀክት ከተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
በዓመቱ እነዚህን እና ሌሎች በዞኑ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት ሲሰራ መቆየቱን የሚናገሩት አቶ ደለለኝ ሻንቆ።
ለአብነት ለሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ማጠናቀቂያ በ1 ዓመት ውስጥ ብቻ 102 ሚሊዮን ብር ክፍያ ተፈጽሟል ነው ያሉት።
ይህም ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ለፕሮጀክቱ ከተያዘው በጀት የተከፈለው 22 በመቶ ብቻ እንደነበር ነው የገለፁት በ1 ዓመት ብቻ 74 በመቶ ክፍያ በመፈጸም ፕሮጀክቱ በታለመለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል ብለዋል።
የአስተዳደርና የሴክተር መስሪያ ቤት የጋራ ህንጻ ግንባታ ማጠናቀቅ ለመንግሥት መስሪያ ቤቶች በየጊዜው ለቤት ኪራይ ተብሎ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ሀብት ማስቀረቱን ተናግረዋል።
በ25 ሚሊዮን ብር ወጪ በ50 ሺህ ካ/ሜ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የሀዲያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል ማክበሪያ ስፍራ "ሀዲይ ነፈራ" ፕሮጀክት በዓመቱ ተግባራዊ ከተደረጉና ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል ነው ያሉት አቶ ደለለኝ።
ከዚህ ውጭ በዞኑ በዓመቱ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በህብረተሰቡ ተሳትፎና በራስ አቅም በየአካባቢው መሰራቱን አስረድተዋል።
በአሁን ወቅትም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ዕቅድ ወጥቶላቸው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሆሳዕና ከተማ የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው 14 ኪ/ሜ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታን ጨምሮ የሾኔና የሆሳዕና ከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ልዩ ድጋፍ በማድረግ ግንባታውን በታለመለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በአጠቃላይ በዓመቱ በዞኑ ለሚገኙ የወረዳና በከተማ አስተዳደሮች የጤና የንጹህ ወጠን ውሃ፣ የትምህርት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታና ለሌሎችም መሠረታዊ ጉዳዮች የዞን ድርሻ ወጪዎችን ጨምሮ 3 መቶ 73 ሚሊዮን ብር የተለያዩ ካፒታል ፕሮጀክቶች ክፍያ መፈጸሙን የገለፁት ኃላፊው
ይህም ለማህበረሰቡ እሴት ለሚጨምሩ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ የተሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ለካፒታል ፕሮጀክቶች ይወጣ የነበረው በጀት በእጅጉ አነስተኛ እንደነበር የሚገልጹት ኃላፊው የዞኑ አስተዳደር ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ ከ5መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ መፈጸሙን ጠቁመዋል።
በዞኑ በዓመቱ ተግባራዊ የተደረጉ የልማት ስራዎች 5መቶ 89 ሺህ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ ስለመቻሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በዞኑ የበጀት አጠቃቀም በቁጠባ ላይ የተመሰረተ ከማድረግ አኳያ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን የሚገልጹት ኃላፊው በተለይም በተሽከርካሪዎች ጥገና የነበረውን አላስፈላጊ ወጪና ጉዞ በማስቀረት በሆሳዕና ከተማ በዘርፉ ለተሰማሩ ድርጅቶች ዕድሉን በማመቻቸት አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ነው ያሉት።
በፊዚካል ፖሊሲና በትብብር መስክ በዞኑ 46 ግብረሰናይ ድርጅቶች ለተከታታይ 5 ዓመታት ተግባራዊ በሚደረጉ 83 ፕሮጀክቶች ላይ ከ1,6 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ በሴቶችና ህጻናት በአካባቢ ልማትና ጥበቃ፣ በግብርና፣ በትምህርትና በጤናው ዘርፍ እየሰሩ እንደሚገኝ የገለፁት ኃላፊው።
ከ1ነጥ 1 ሚሊዮን በላይ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውና ከ3መቶ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በተያዘው የ2015 በጀት ዓመት አስተዳደራዊ ወጪዎችን በመቀነስ ተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መጀመር ሳያስፈልግ ለረዥም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ የሆኑና ያልተጠናቀቁ ካፒታል ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።