በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት የአራዳ ቀበሌ የሴቶች አደረጃጀቶች ከቀበሌ አስተዳደሩ ጋር በመሆን ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጳጉሜ 02/2014 ዓ.ም
የሀዲያ ዞን ም/አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ታፈር ፣ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤልታደሰ ፣ የዞን ፣ የከተማ ፣የቀበሌ አስተዳደርና ሌሎች የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በስንቅ ዝግጅቱ ላይ ተሳትፈዋል ።
የከተማ አስተዳደሩና የቀበሌዉ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ስንቅ እያዘጋጁ ያሉ የሴቶች አደረጃጀትን በጉልበት በማገዝ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት አጋርነታቸውንም እየገለፁ ይገኛሉ ።
የሀዲያ ዞን ም/አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ታፈራና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ታደሰ በየበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩና የቀበሌው ህዝብ ለ6ኛ ዙር ለህልውና ዘመቻው በሁሉም ግንባሮች ተሰልፈ ሀገርን በማደን ለሚገኙ ሠራዊት ሀብት ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በመሰብሰብ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው የተጀመረው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡
አክለውም ኃላፊዎቹ የስንቅ ዝግጅቱ የሀገርን ሕልውና ለማስከበር ከፊት ተሰልፎ የሕይወት መሰዋእትነትን በመክፈል ላለው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አለኝታነታችንን ማሳያ ነዉም ብላዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በርከት ታደሰና የአራዳ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብዙነሽ ብርቄ ባስተላለፉት መልዕክት የሀገርን ሕልውና የማስከበር ዘመቻ ተልዕኮውን ይዞ በመከላከል ላይ ያለው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የመደገፉ ስራ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ጠቁመው በሀገር የመጣውን ጠላትን በመመከት የሕይወት ዋጋ በመክፈል ላለው ለመከላከያ ሠራዊት አቅም በሚችሉት ሁሉ ለማገዝ እና ከጎኑ ለመቆም መነሳታቸውን በመግለፅ መጠነ ሰፊ የስንቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው ስሉ ገልፀዋል ።