16
Sep
2022
በሆሳዕና ከተማ የሴች ዱና ቀበሌ አስተዳደር ያሆዴ መስቀላ የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓልን ምከንያት በማድረግ የጽዳት ዘመቻ አካሄደ ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም 06 /2015 ዓ.ም
በፕሮግራሙ ላይ የዞን፣ የከተማና የቀበሌው አመራር አካላት እና ፣ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተደደር ም/ ከንቲባ አቶ በየነ ሸንቆና የሴች ዱና ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ከሣ በየበኩላቸው በከተማችን ዘርፍ ብዙ ተግባራት እየተሠራ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል ።
አክለውም በከተማችን በሚሠሩ መሠረተ ልማቶች ላይ የሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን አስተኦጽኦ ማድረግ የጎላ ሚና መኖሩን በመገንዘብ በጽዳት ዘመቻና በሌሎችም ተግባራት ላይ በንቃት በመሳተፍ በማስዋብ የተጀመረውን ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል ።