።።።።። መስከረም 6/2015 ዓ.ም።።።።።።( የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
የሀዲያ ልማት ማህበር ዋና ሥራአስኪያጅ የሆኑት አቶ አድነው ሎንሰቆ እንደተናገሩት መንግስት ሲሚንቶ እንደ አንድ ሸቀጥ ከፍተኛ እጥረትና ዋጋ ንረትን በመቆጣጠርና ዋጋ በመተመን ለተጠቃሚዎች በመከፋፈል የኮንስትራክሽን ዘርፉ እንዳይዳከም እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው
የሀዲያ ልማት ማህበር እንደ አንድ የሕዝብ ልማት ማህበር የመንግስት መመሪያውን ደንቡን በመከተል የመንግስት ፕሮጀክቶች እና የግል ባለሀብቶች ግንባታቸው እንዳይስተጓጎል ስሚንቶን ከፋብሪካው በመስጠት የቆሙ ግንባታዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እንዲገቡ እየተደረገ ይገኛል።
አክለውም መንግስት በወጠው መመሪያና ዋጋ መሠረት የተጠቃሚዎችን ችግርና እንግልት ለመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነም ተናግረዋል።
በሆሣዕና ከተማ ያነጋገርናቸው ግንባታ ላይ ያሉ ባለሀብቶች መካከል አቶ መሠለ ፎርሲዶና አቶ መውለድ ጠንክር በበኩላቸው የሲሚንቶ እጥረትና ዋጋ ንረት በመኖሩ ምክንያት ግንባታቸው ተቋርጦ መቆየቱን አስታውሰው
መንግስት የሀገሪቷን ሠላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የግንባታ ፕሮጀክቶች ፣የልማት ሥራዎችና የግል ባለሀብቶች ግንባታ ሥራ እንዳይቋረጥ ሲሚንቶ በልማት ማህበር በኩል እንዲቀርብ መደረጉ ለኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ እያደረገ ያለው ጥረት የሚያበረታታ መሆኑን ጠቅሰው
የሲሚንቶ እጥረት እንዳይኖር ባለድርሻ አካለት ተቀናጅተው በትኩረት መስራት እንዳለባቸውን አስተያየታቸውን አጋርተዋል።
በጫኬቦ ኤርጫፎ