17
Sep
2022
"ያሆዴ" በዓልን ማስተዋወቅና ህዝባዊ መሠረትን ማጎልበት ዓላማ ያደረገው "ቱር ያሆዴ" በተለያዩ የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ተካሄደ ።
"ያሆዴ" የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን በብሄሩ ተወላጆች ዘንድ ተወዳጅና ተጠባቂ በዓል ነው።
በዓሉን መጪው መስከረም 14 በዞኑ መዲና በርካታ የዞኑ ህዝብ በተሳተፉበት በልዩ ድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
የቅድመ ዝግጅቱ አካል የሆነውና ቱር ያሆዴ በተለያዩ የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ተካሂዷል።
የዞኑ የባህል ቡድን፣ የተለያዩ ግለሰቦችና የመንግስት አካላት የተሳተፉበት "ቱር ያሆዴ" በምዕራብ ባደዋቾ፣ በሾኔ ከተማ አስተዳደር፣ በምስራቅ ባደዋቾና በሻሾጎ ወረዳዎች ተዘዋውረው ማህበረሰባዊ ንቅናቄ አድርገዋል።
የዞኑ የባህል ቡድን በተዘዋወሩባቸው ከተማዎች ሁሉ በህዝቡና በመንግሥት አካላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
"ቱር ያሆዴ" ያሆዴ በዓል ይበልጥ ህዝባዊ መሠረት እንዲይዝ ያለመ ሲሆን ከዛ ባሻገር ያሆዴ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ ነው።
የሀዲያ ዞን አስተዳደር በዞኑ ባሕልና ቱሪዝምና በቱር ያሆዴ አዘጋጅነት የተካደ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ በሌሎች የወረዳና የከተማ አስተዳደር ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።