የ "ያሆዴ" በዓል አከባበር ስርዓተ ክዋኔና እሴቶቹን በይበልጥ በማሳወቅ ሕዝባዊ መሠረቱን በማጠናከርና በማልማት በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሠራ ነው__የሀዲያ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ

መስከረም 11/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

የሀዲያ የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል አከባበር ስርዓተ ክዋኔና እሴቶቹን በይበልጥ በማሳወቅ ሕዝባዊ መሠረቱን በማጠናከርና በማልማት በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሠራ እንደሚገኝ የሀዲያ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ገለጸ።

የሀዲያ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እርስቱ ለ2015 ዓ.ም የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓልን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በዓሉን በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት (በዩኔስኮ) ለማስመዝገብ እየተሠራ መሆኑን ገለፃዋል።

ያሆዴ የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ከጭጋግና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከ አ ሮጌ ው ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሻገ ሪያ ነ ው ያሉት አቶ ተስፋዬ።

ያሆዴ የአዲስ ዓመት ብርሃ ን ማብሰሪያ፣ በተለያየ ምክንያት ከአካባቢው እርቀው የሚኖሩ ወገኖች ከወላጆቻቸው ጋር የሚገናኙበት፣ የተጣላ የሚታረ ቅበ ት፣ ታላቅ ክብረ በዓል ነው ብለዋል።

በመሆኑም ባህሉ በይበልጥ እንዲጠናከር እንዲጎለብት እንዲሁም ይዘቱ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተተገበሩ መቆየቱን የገለፁት ኃላፊው።

ለዚህም የበዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሆነው "ሀዲይ ነፈራ" ለምቶ ለዘንድሮ በዓል መድረሱና በዓሉ ባህላዊ ይዘቱ ተጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማስቻል ጥናት ተካሂዶ ዶክሜንት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በዚህም መነሻነት ያሆዴ በዓል በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘንድሮ ዓመት መስከረም 14/2015 ዓ.ም በሀዲይ ነፈራ ላይ በድምቀት የሚከበረው የያሆዴ ክብረ በዓልም የዚሁ ማሳያ ነው።

በመሆኑም ሁሉም የብሔሩ ተወላጆችና ወዳጆች በዓሉን በነቂስ ወጥቶ እንዲያከብርና ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ለሀዲያ ህዝብና ለመላዉ ለኢትዮጵያውያን

እንኳን ለ2015 ዓ.ም የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር ፣የ መቻቸል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገለፀዋል ።

Share this Post