"ያሆዴ" በዓል በሰላም እንዲከበር ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

መስከረም 11/ 2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

የሀዲያ የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የሀዲያ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ተሾመ ባቲሶ

በሰጡት መግለጫ በዓሉን በምናከብርባቸው ስፍራዎች የጸጥታና የደህንነት ጥበቃ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡

በዓሉ ሲከበር በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲከበር ከሆሳዕና ከተማ፣ ከሌሞ ወረዳ የፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የከተማው ነዋሪዎችም ሆነ የበዓሉ ታዳሚዎች አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከቱ የመምሪያው የመረጃ ስልክ ቁጥሮች 0465550330 እና 0465553211 ደውሎ መረጃ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ አቅርቧል፡፡

በዓሉ ከትራፊክ አደጋ የጸዳ እንዲሆን በተቀናጀ መልኩ የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ የገለጹት ዋና አዛዡ የትራፊክ ደንብ አስከባሪዎች በየመስመሩ ተመድበው የትራፊክ ፍሰቱ ሰላማዊ እንዲሆን እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ተሾመ ባቲሶ ለመላው የሀዲያ ህዝብና ለፖሊስ አባላት እንኳን ለያሆዴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

Share this Post