መስከረም 12/2015 ዓ/ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
በዓሉ በወረዳ ደረጃ ስከበር የወረዳው የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ፣የሀገር ሽመግሌዎች፣ተጋባዥ እንግዶች ፣የአከባቢው ተወላጆች እና ሌሎችም አካላት ተሳትፈዋል ።
በበዓሉ መክፈቻ የምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል ።
የሀድያ ብሔር የራሱ የሆነ ታሪክ ፣ባህል፣ቋንቋ ፣ወግ እና ልማድ ያለው ሕዝብ መሆኑን የተነገሩት አስተዳዳሪ የ"ያሆዴ"በዓል አከባበር ሕዝባዊ መሠረት ያለው በመሆኑ በብሔሩ ዘንድ ከሚከበሩ በዓለት መካከል ልዮ ያደርገዋል ብላዋል።
በዓሉ ያለፈውን አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አድስ ዓመት የምንቀበልበት ፣የአብሮነት ፣የመቻቻል ፣የፍቅር እና የአንድነት ባህላችንን ይበልጥ የምናጠነክርባት ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል ።
በወረደው የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን በዶሬ በበኩላቸው "ያሆዴ" የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል አድስ ዓመት በአድስ መንፈስ የምንቀበልበት ከመሆኑም በሸገር በዓሉ አንድነታችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ፣የተጣሉትን የሚያስታርቅ የሠላም በዓል መሆኑን በማብራራት ዓመቱ የሠላም፣የጤና ፣የፍቅር እና የብልፅግና ዘመን እንድሆን ያለቸውን ምኞት ገልጸዋል ።
በክብረ በዓሉ ላይ በ"ያሆዴ" በዓል ወይይት በማድረግ ፣የሀድያ ባህል ጨዋታ በማድረግ እና በተለያዩ ዝግጅቶች በወረዳው ተክብሯል።
ምንጭ:- የወረዳው ኮሙኒኬሽን