የፋይናንስ የገቢዎችና የፕላን መምሪያዎች ለሀዲያ ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ ልማት መምሪያ ለ2015 ዓ.ም የሀዲያ ህዝብ ዘመን መለወጫ በዓል ‘ያሆዴ’ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
ይህ በዓል የሀዲያ ህዝብ አዲስ ራዕይ እቅድ የሚያወጣበት ክረምቱ አልፎ ከጨለማ ወደ ብርሀን የሚሸጋገሩበት የተጣለው የሚታረቅበት ሰው እንስሳቱ የሚጠግብበት ህዝባዊ መሠረት ያለው ትልቅ በዓል መሆኑን የገለፁት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ አቶ ደለለኝ ሻንቆ።
በዓሉ እንደ ሀገር እየተሸረሸረ የመጣውን መቻቻልና መደጋገፍ በማስቀጠል በህብረተሰብ መካከል በጋራ መልማትን የሚያጠናክር እሴት በመሆኑ በቀጣይ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በሰፊው እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የሀዲያ ዞን ገቢዎች መምሪያ ለ2015 ዓ.ም የሀዲያ ህዝብ ዘመን መለወጫ በዓል ‘ያሆዴ’ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
‘ያሆዴ’ የሠላም የአንድነት መገለጫ የሆነ ልዩነቶች የሚወገዱበት የአብሮነታችን እሴት የሚጠናከርበት ልዩ የሀዲያ መገለጫ መሆኑን የተናገሩት የሀዲያ ዞን ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ መሳይ ተስፋዬ ናቸው።
የሀዲያ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ለ2015 ዓ.ም የሀዲያ ህዝብ ዘመን መለወጫ በዓል ‘ያሆዴ’ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተልፏል
የሀዲያ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ጥላሁን ሞላ የሀዲያ የዘመን መለወጫ ‘ያሆዴ’ በዓል ከጥንት ጀምሮ በልማትና መልካም አስተዳደር ለህብረተሰቡና ለመንግስት የጎላ ሚና እያበረከተ ያለ ባህላዊ ዕሴት መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ ለመላው በሀገርና በውጭ ለሚኖሩ የማህበረሰቡ ተወላጆች የእንኳን አደረሳችሁ መመልዕክት አስተላልፈዋል።
የመምሪያ ኃላፊዎቹ በሀገርና በውጭ ለሚኖሩ የሀዲያ ተወላጆችና ለመላዉ ኢትዮጵያን የእንኳን ‘ለያሆዴ’ በዓል በሠላም አደረሳችሁ መመልዕክት አስተላልፈዋል።