የአንሌሞ የምዕራብ ሶሮ ወረዳዎችና የቦነሻ ከተማ አስተዳደር ለያሆዴ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳደሪው አቶ ሊሩ ጀማል ለሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘’ለያሆዴ’’ በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

‘’ የያሆዴ በዓል’’የሀዲያ ህዝብ ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚነገርበት እና አዲስ ተስፋ የሚሰንቅበት በዓል መሆኑን የተናገሩት አቶ ሊሩ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለሀዲያ ብሔር ተወላጆችና ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የምዕራብ ሶሮ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ዘለቀ ዶሌቦ ለሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉ ባህላችንን የምናሳድግበትና አንዳችን ለአንዳችን የምንተሳሰብበት በዓል ይሁንልን ብለዋል።

በሀዲያ ዞን የቦኖሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታምራት ደሳለኝ የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓልን አስመልክቶ ለመላው የቦኖሻ ከተማ ህዝብ እነ የሀዲያ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዓሉ የሰላም ፥ የፍቅር፥ የአንድትና የመደጋገፍ እንዲሆንም ተመኝተዋል።

ምንጭ:- የአንሌሞ፣ የምዕራብ ሶሮና የሻሾጎ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

Share this Post