የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት <<ወጣቶችና መሪነት>> በሚል ርዕስ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት <<ወጣቶችና መሪነት>> በሚል ርዕስ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሀሴ 06/2014 ዓ.ም

በስልጠናዉ ከስድስቱ ቀበሌያት ከተለያዩ የወጣት አደረጃጀቶች የተዉጣጡ ከ80 በላይ የሆኑ በወጣቶች ስብዕና ማዕከል አዳራሽ እየተሳተፉ ይገኛል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሰሀ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናዉ

ኀብቁ ፣ ተወዳዳሪና ተፅኖ ፈጣሪ ሆነዉ ሀገርና እራሳቸዉን እንዲጠቅሙና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሀድ አዳዲስ ልምዶችን ከመፍጠርና ከማነቃቃት አንፃር ስልጠናዉ ያለዉ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በንቃት እንዲከታተሉ አሳበዋል።

ሰልጣኝ ወጣቶች በበኩላቸዉ ባገኙት ግንዛቤ ራሳቸዉን ብቁ ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደሚረዳቸዉና በተለይ ስለ መሪነት ያገኙት ግንዛቤ ወደፊት አርቀን እንድናይ የሚደረገን ስለጠና ስሉ ነው ተናግረዋል።

Share this Post