በአዲሱ ዓመት ልብሳችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም አስተሳሰባችንና አገልግሎት አሰጣጣችንም አዲስ መሆን አለበት ሲሉ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ ተናገሩ።
ዋና አስተዳዳሪው ይህን ያሉት የሀዲያ ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓልን በማስመልከት የባሕልና የፎቶ ኤግዝቢሺን በተካሄደበት ወቅት ነው።
ኤግዚቢሺኑ በዞኑባሕል ቱሪዝምና በመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ትብብር የተዘጋጀ ነዉ።
በኤግዝብሺኑ የዞኑ ወረዳዎች የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ የሀዲያን ባህል የሚገልፁ ቁሳቁሶች የተሰናዱ ሲሆን ይህም በዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል።
በኤግዝቢሺኑ መክፈቻ ወቅት የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ አብርሃም መጫ ባስተላለፉት መልዕክት በሀዲያ ባሕል ትልቅ ቦታ ተሰጥቷቸዉ ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ያሆዴ ነዉ።
በዓሉ ከዘመን መለወጫ ጋር አብሮ የሚመጣ በመሆኑ በዓሉን ሲናከብር አሮጌ አስተሳሰብንና አካሄድን ወደኋላ በመተዉ ከአዲሱ ዓመት ጋር የምንጓዝበትን መንፈስ የሚንታደልበት ነዉ ብለዋል።
በአዲስ ዓመት ልብሳችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም አስተሳሰባችንና አገልግሎት አሰጣጣችንም አዲስ መሆን አለባቸዉ በማለትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ የዞን የወረዳዎችና የከተማ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን መስከረም 14/2015 በሀዲይ ነፈራ በሚከበረዉ የያሆዴ በዓል ሁሉም የብሔሩ ተወላጆችና ወዳጆች ተገኝተዉ አንዲያከብሩ ጥሪ ቀርቧል።
በኤልያስ ተሰማና በደገለ ባምቦሬ