23
Sep
2022
መስከረም 12/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
የፎንቆ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለሙ አህመድ የሀዲያ ዘመን መለወጫ የሆነው የያሆዴ በዓል በብሄሩ ወጣቶች፣ አባቶች፣ ሴቶችና ህጻናት ዘንድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚከበር ታሪካዊ በዓል መሆኑን ተናግረዋል።
የከተማው አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፍ መሃመድ ለፌቦ በየአመቱ የሚከበረውን ያሆዴ የሀዲያ ዘመን መለወጫ በአል በብሄሩ ታሪክ ልዩ ትርጉም ያለውና ከኢትዮጵያ ባህሎችና ቅርሶች አንዱ በመሆኑ በዩኒስኮ ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በበዓሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማው አስተዳደር ከንቲባው አቶ ሸምሰዲን ቲርኡሎ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሆነው ህወሓት ሀገርን ለማፍረስ የከፈተውን ጦርነት በመመከት ያሆዴን የሀዲያ ዘመን መለወጫ በአልን ማክበር ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል።
ያሆዴ የሀዲያ ዘመን መለወጫ በአል የሀይማኖት ልዩነት ሳይኖር የሚከበር የብሄር የማንነት መገለጫ ነው ብለዋል።
በአሉን ለማክበር የነበረውን አንድነት ሀገርን ከጠላት ለመታደግና ለልማት የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም ከንቲባ ሸምሰድን አሳስበዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙ የከተማው ነዋሪዎችም በአሉን በደስታ፣ በፍቅር ፣በአንድነትና በመተሳሰብ ማክበራቸውን ተናግረዋል፡(ደሬቴድ)