23
Sep
2022
የሀዲያ ዞን የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጸጋው ሙልጌታ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል መኮሮ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲሴ አውቶ ያሆዴ በዓልን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የተከበራችሁ የሀዲያ ተወላጆችና ወዳጆች እንዲሁም መላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2015 ዓ.ም ለሀድያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን!!
የያሆዴ በዓል በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉ በዓል ነው። ለዚህም በብሔሩ ባህል መሠረት አባቶች፣ እናቶችና ልጆች የየራሳቸዉን ዝግጅት በማድረግ በጉጉት የሚጠብቁት ትልቅ በዓል ስለመሆኑም ገልፀዋል
በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የአካባቢያችንን ብሎም የአገራችንን ሰላምና ደህንነትን በጋራ በመጠበቅ ሊሆን ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
በዓሉ የሠላም፣ የይቅርታ፣የአንድነትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞታችን ገልጸዋል።
በኤልያስ ተሰማ