የፍትህ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የሴቶችና ህጻናት መምሪያዎች የሀዲያ ዘመን መላወጫ "ያሆዴ" በዓልን አስመልክቶ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የሀዲያ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሀብታሙ ሌንጆሬ

"ያሆዴ" በዓል በሀዲያ ብሔር በድምቀት የሚከበርና የአንድናትና የአብሮነት ጥንካሬ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ እንዳሉት "ያሆዴ" በማህበረሰቡ ዘንድ በግጭትና በተለያዩ ምክንያቶች ተለያይቶ የከረሙ ህብረተሰብ ክፍል በመቀራረብ እርቅ የሚደረጉበትና አብሮነት የሚታይበት በዓል በመሆኑ ፋይደው የጎላ ነው ብለዋል።

የሴቶችና ህፃናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ስመረት ሳሙኤል

ያሆዴ የፍቅር የአንድነት በዓል እንደመሆኑ እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ በመስተሳሰብ፣ በመረዳዳትና በየምናሳልፍበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ዓመቱ የሰላምና የብልጽግና እንዲሆን በመመኛት ለመላው ሀዲያ ህዝብ ኢትዮጵያውያን ለዘመን መለወጫ "ያሆዴ" እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

በደገለ ባምቦር

Share this Post