የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፏዋል ።

የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መስከረም 16/2015 ዓ.ም

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ እዮብ ባስተላለፉት መልክት የመስቀል ደመራ በዓል ለህዝቦች መቀራረብ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ።

አቶ አሸናፊ አክለውም በዓሉ የጥል ግድግዳ ተንዶ የዕርቅ ስርዓት የሚከናወንበት ታላቅ በዓል መሆኑን ጠቁመው ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የአብሮነትና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፏል።

Share this Post