በሆሳዕና ከተማ የቦቢቾ ቀበሌ የገቢዎች በ/ቅ/ጽ/ቤት ከከተማው ገ/በ/ቅ/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በተለያዩ ንግድ ለተሰማሩ ለደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በግብር ምንነት ፣ በግብር ዓይነቶችና የግብር አከፋፈል ዙርያ ስልጠና ተሰጠ ።

የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት 03/2015 ዓ.ም

በስልጠና ላይ የቀበሌው አመራር አካላት፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፣የከተማው ጽ/ቤት የምጣኔ ጥናት የታስክ ትምህርትና ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክተሮት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።

የቦቢቾ ቀበሌ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ አለማየሁ እንደገለፁት መንግስት በፋይናንስ ምንጭነት ከሚጠቀምባቸው አንዱና ዋነኛው ግብር መሆኑን ጠቁመው ግብር ከነዋሪው ህብረተሰብ ተሰብስቦ ለራሱ ለህብረተሰቡ ለመሠረተ ልማቶች ሥራ የሚውል ጥሪት /ሀብት/ ከመሆኑ አንጻር የግብር ጉዳይ የግብር ሰብሳቢ ብቻ አለመሆኑን በመረዳት የመላ ህብረተሰብ ነዉ ስሉ ገልጸዋል ።

አክለውም ኃላፊው ግብር መክፈል እንደሚገባ ማመን ብቻ ሳይሆን ከስወራና ከማጭበርበር በፀዳ መልኩ ትክክለኛውን ገቢ በማሳወቅ በተደነገገው ጊዜ ውስጥ መክፈል እንዲችል ሁሉም ማህበረሰብ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

Share this Post