በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት የተጀመረውን የሀገሪቱን ለወጥ መስቀጠል አማራጭ የሌላ ተግባር መሆኑን የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት የተጀመረውን የሀገሪቱን ለወጥ መስቀጠል አማራጭ የሌላ ተግባር መሆኑን የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ

ኮሌጁ በተለያዩ ሙያ መስኮች ለ19ኛ ዙር በደረጃ ያሰለጠናቸውን 1361ተማሪዎችን አስመርቋል ።

።።።።።።።።። ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም ።።።።።።( ሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

ኮሌጁ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በተለያያ ሙያ መስኮች ሰልጣኞችን ተቀብሎ በማሰልጠን በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የእለቱ ክብር እንግዳ የደቡብ ክልል የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታመነ ገብሬ እንደተናገሩት ትምህርትና ስልጠና ለአንድ ሀገር እድገት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።

ዜጎች የቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅምን ለማሳደግ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ሚናቸው የጎላ ነው።

የኮሌጁ ቀዳሚ ተግባር የኢንዱስትሪውን የሰው ሀይልና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለይቶ በማወቅ በኢንዱስትሪ ፍላጎት መሰረት የሚፈለገውን ብቃት ያለውን የሰው ሀይልን ማፍራት ነው ብለው

በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ በመሆን የትኛውንም ስራ ሳይንቁ ከትንሽ በመጀመር ትልቅ ቦታን የመድረስ ህልምን ይዘው ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል በታማኝነት እንዲያገለግሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኮሌጁ ዲን አቶ አወል ሸንጎ እንደተናገሩት የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍን ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ ኮሌጁ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

ኮሌጁ ለ19ኛ ዙር በመደበኛና በማታ ትምህርት መርሃ ግብር በ21 ትምህርት አይነቶች ያሰለጠናቸውን ሴት 797 ወንድ 564 በአጠቃላይ 1 ሺህ 3 መቶ 61 ተማሪዎችን በደረጃ ከ2 እስከ 5 ሰልጣኞችን ማስመረቁን በመግለጽ፣

ተመራቂዎችም ሀገርንና ህዝብን በታማኝነት እና በቅንነት እንዲሁም በበጎ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ከህዝብና መንግስት ጎን በመቆም የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት ሌላኛው ክብር እንግዳ የሀዲያ ዞን ምክትል አስተዳደርና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀገዬ ተረፋ እንደገለፁት የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግና ሊረጋገጥ የሚቻለው የሰለጠነ የሰው ስኖር እንደሆነ ተናግረዋል ።

ተመራቂዎች በበኩላቸው በኮሌጅ ቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና ክህሎትን በመጠቀም ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ በመሆን በሰለጠኑበት ሙያ መስካቸው የቴክኖሎጂ ሽግግርንና የፈጠራ ስራቸዉን ለማህበረሰቡ በማድረስ በታማኝነትና በቅንነት ህብረተሰቡን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በአድነው አሰፋ

Share this Post