በሆሳዕና ከተማ የአራዳ ቀበሌ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ከከተማው ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በተለያዩ ንግድ ለተሰማሩ ለደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በግብር ምንነት ፣ በግብር ዓይነቶችና በግብር አከፋፈል ዙርያ ስልጠና ተሰጠ ።

የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት 08/2015 ዓ.ም

የአራዳ ቀበሌ አሰተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድነው ሰዴቦ እንደገለፁት መንግስት ግብር ከነዋሪው ህብረተሰብ ሰብስቦ ለራሱ ለህብረተሰቡ ለመሠረተ ልማቶች ሥራ እንደሚያውለው ግንዛቤ በመያዝ ሁሉም ዜጋ ለግብር አሰባሰብ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ።

አክለውም በቀበሌው በ2014ዓ.ም ግብር አከፋፈል ወቅት የአራዳ ቀበሌ ግብር ከፋዮች የሚፈለግባቸውን የመንግስት ግብር በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው በማጠናቀቅ ላሳዩት አርአያነት ያለው ተግባር በማመስገን በግብር ስወራ ዙሪያ የሚፈፅሙ ህገ-ወጥ ተግባራት በማጋለጥ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል ።

Share this Post