የሆሳዕና ከተማ የካቢኔ አባላት የሴክተር መ/ቤቶች አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም በከተማው በግብርናው ዘርፍ በመኸር ወቅት በግለሰብ እና በተቋማት የተከናወኑ የሰብልና የጓሮ አትክልት ምርቶች ጎብኝተዋል።

ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም

የአመራር አካላቱ ከዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በኋላ ተዟዙረው ከተመለከቱዋቸው ማሳዎች መካከል በአራዳ ቀበሌ አስተዳደር በቢር ዋቸሞ ት/ቤት ከ3 ሄክታር በላይ የለማ የምስራች የገብስ ዘር እና በሊች አምባ ቀበሌ በወጣቶች በማህበር የለማ የጓሮ አትክልት ይገኙበታል ።

Share this Post