31
Oct
2022
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም
በውይይቱ ላይ በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ፐብሊክ ሠርቫንት በሙሉ ተሳታፊ በመሆን በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ የውይይት መድረክ እየተደረገ ነዉ ።
የሆሳዕና ከተማ የፐብሊክ ሠራተኞች "በደም የተከበረ፣ በላብ የታሰረ"በሚል ሀሳብ ኢትዮጵያን ከውስጥና ከዉጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ለመጠበቅ ሁሉም ሠርቨንት የበኩላቸውን ኃላፊነት ልወጣ የሚያስችል ለውይይት የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑን ተገልጸዋል ።
በሶስቱም መድረኮች የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት ለስልጠና የተዘጋጀውን ሰነድ ገለጻ እየተደረገ ነዉ ።
ኢትዮጵያ በአባቶቻችንና በእናቶቻችን ደምና አጥንት መስዋዕትነት የተገኛውን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ክብርና ነፃነትን በመጠበቅ ድህነትን በላብ በማሸነፍ ሉዓላዊነታችንን ማፅናት ላይ ያተኮረ ስልጠና መድረክ መሆኑንም ተጠቅሰዋል ።
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር በመተባበር የሚሠሩት እኩይ ተግባር ለማምከን በደም የተከበረውን ኢትዮጵያን በላብ ለማስተሳሰር የበኩላቸውን አስተኦጽኦ ለመወጣት የሚያስችል ውይይት መሆኑን ተጠቁመዋል ።