"በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር "በደም የተከበረ፣ በላብ የታሰረ" በሚል መሪ ቃል የአመራሮች ስልጠና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም

በመድረኩ ላይ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሊሬ ጀማልና አጠቃላይ አመራር ፣ የቀበሌ አመራር አካላትና መሠረተ ድርጅት አመራሮችን ጨምሮ ያሳተፈ መሆኑን ተጠቁሟል።

የሆሳዕና ከተማ አመራሮች "በደም የተከበረ፣ በላብ የታሰረ" በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የሀዲያ ዞን ገ/በ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ተስፋዬ ለስልጠና የተዘጋጀውን ሰነድ ገለጻ እያደረጉ ናቸው።

የከዚህ በፊት በአባቶቻችንና በእናቶቻችን ደምና አጥንት መስዋዕትነት የተገኛውን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ክብርና ነፃነትን በመጠበቅ ድህነትን በላብ በማሸነፍ ሉዓላዊነታችንን ማፅናት ላይ ያተኮረ ስልጠና መድረክ መሆኑንም ተገልጸዋል ።

አሸባሪው ህወሓትና ኦነግ ሻኔ ቡድን ከውጭ ሴራኞች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየሰሩ እንደሚገኙ በማንሳት የመጣንበትን መንገድ በተገበው በመረዳት በሚፈልገው መንገድ ለመመከትና በደም የተከበረውን ኢትዮጵያን በላብ በመታሳሰር የበኩላቸውን አስተኦጽኦ ልወጡ የሚያስችል የስልጠና

መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል ።

Share this Post