ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር በትምህርት ስርዓት ላይ ችግር ፈቺ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል_ አቶ አብርሃም መጫ
ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር በትምህርት ስርዓቱ ችግር ፈቺ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ ተናገሩ።
ነሐሴ 2/2014 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዕቅድ ቅድመ ዝግጅት ተግባር አፈጻጸም ዙሪያ ከዞን ፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮችና ትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በሆሳዕና ከተማ ምክክር ተደረገ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ የትምህርት ስርዓቱ በተለያዩ ምክንያቶች ያጋጠመውን ስብራት ለማከም ብሎም በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር ችግር ፈቺ የሆኑ ድጋፍና ክትትል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል።
ማስረጃን እንጂ እውቀትን በገንዘብ መግዛት ስለማይቻል ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ልጆቻችን የሀገር የሚያስቀጥሉ የዚህች ሀገር ተስፋ እንዲሆኑ መስራት ይጠበቃል።
ወላጆቻችን ሳይማሩ አስተምረውን በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ልጆችን መፍጠር ከቻሉ ከተማርነው ከእኛ የተሻለ ውጤት ይጠበቃል ያሉት አቶ አብርሃም።
እውቀት ሌላኛው የአለማችን ህዝቦች ቅኝ መግዣ መሳሪያ በመሆኑ ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት በመስጠት መስራት ለነገ ዋስትና መሆኑን በመረዳት የዞኑን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።
የሀዲያ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጌታቸው ለሊሾ የትምህርት ጥራት ላይ የሚታየው ችግር ለመቅረፍ በዝግጅት ምዕራፍ ትምህርት ቤቶችን በበቂ መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ከትምህርት ተቋም ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በየደረጃው ያለው በተለይ ከተማሪ ወላጆችና መምህራን ጋር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር አበበ ሎላሞ የመድኩ አላማ በ2014 ዓ.ም የታዩ ተግዳሮቶችን ከትምህርት ዘርፉ ባለድርሻ ጋር በጋራ በማረም በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር መሆኑን ገልፀው።
ለትምህርት ውጤት መውረድ የአንድ ጀምር ችግር ብቻ ሳይሆን ለቅድመ መደበኛ የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ መሆን የመማር ማስተማር ሂደት ቁጥጥር ችግርና ሌሎችም በርካታ የአሰራር ጉድለት ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።
በ2015 ዓ.ም የአዲሱ ፍኖተ ካርታ ትምህርት ዝግጅት ትግበራን ጨምሮ በአዲስ መልክ 8ተኛ ክፍል መልቀቂያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን የ6ተኛ ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ ክልላዊ ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ጠንከር ያለ የትምህርት ዝግጅት ከመምህራንና ከተማሪዎች እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።
ለዚህም ለቅድመ መደበኛ የደረሱ ህፃናትን የመለየትና የመማሪያ ተቋም የመገንባት ስራ መሰራቱን የተናገሩት ሀላፊው የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተለያዩ የትምህርት ማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ እንዳለ አስታውቀዋል።
በቀጣይ ከሀሰተኛ መረጃዎች እና ከተፈቀደላቸው ውጭ የሚያስተምሩ የትምህርት ተቋማትን የማስተካከል እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀው የሁሉን እርብርብ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመምህራን ብቃት ምዘናው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መምህራን በተቋሙ ተተክለው እንዲሰሩ መደረግ እንዳለበት አስተያየት ተሰጥተዋል።
የተማሪዎች ስነምግባር ላይ ትኩረት በመስጠት መሰራት እንዳለበት የገለፁት አስተያየት ሰጪዎች የትምህርት የሱፐርቪዥን ስራው ጠንካራ መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል።
በምክክር መድረኩ የዞን ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ፣ ርዕሰ መምህራንና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በኤልያስ ቲርካሶ
318Wondimu Defar, Mulatu Sule Ertiro and 316 others
20 Comments
42 Shares
Like
Comment
Share