የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በትምህርት መሻሸል መርሀ ግብር እና በት/ቤቶች ደረጃ ምደባ እስታደርድ አመላካቾች ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ።

ህዳር 2/2015ዓ.ም

በስልጠናው ላይ የግልና የመንግሥት ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራን ፣ሱፐር ቫይዘሮ፣ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አዳነ ዘመድኩን በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ት/ቤቶች ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ በማድረግ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ውጤት በማሸጋገር የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

Share this Post