አስር ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄን ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ

አስር ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄን ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚገኙ አሥር ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄን ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

ጥያቄውን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተቀብለዋል። ምክር ቤቱ ውሳኔውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳውቃልም ብለዋል።

የአሥሩ ዞኖች እና የሥድስቱ ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች በክልል መደራጀታችን የህብረተሰቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታትና አብሮነትን ማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ነው ማለታቸውን ፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

በክልልነት እንደራጅ ብለው ጥያቄያቸውን ያቀረቡት 10 ዞኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

ወላይታ፣ጋሞ፣ጎፋ፣ኮንሶ፣ደቡብ ኦሞ፣ጌዴኦ ዞኖች፣እንዲሁም ደራሼ፣ባስኬቶ፣ኸሌ፣አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች አንድ ላይ በክልል እንደራጃለን ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል ስልጤ ፣ከምባታ ጠምባሮ፣ሀዲያ ፣ሀላባ፣የም ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ በክልል ለመደራጀት በየምክር ቤቶቻቸው በማጽደቅ መወሰናቸው ይታወሳል።

Share this Post