05
Sep
2025
ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ፣ የመንግስት የማስፈፀም አቅም በማጎልበት ለጠንካራ ሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ታምኖበት በተሰራው ሥራ ሀገራችን የጀመረችው የከፍታ ጉዞ ወደ ማንሰራራት የሚያደርሱ በርካታ ተምሳሌታዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችለናል።
የተደረገው ውይይት ፓርቲያችን የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ የሰነቀውን ዓላማ እውን ለማድረግ በአመራሩ ዘንድ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት የፈጠረ መሆኑ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
በየደረጃው የሚገኘው አመራርችን ወቅታዊ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በመረዳት የፓርቲያችንን ተልዕኮ በተቀናጀ መልኩ በብቃት ለመፈፀም አቅም እንደሚሆን በአመራሮቹ ተነስቷል።
በመጨረሻም ሁሉም አመራር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰማራበት መስክ ሁሉ አርበኛ መሆን እንዳለበት የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱ ተቋጭቷል።
ዘገባው የሆሳዕና ከተማ ብጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ነው ።