በሆሳዕና ከተማ የጤና ስፖርት ማህበር የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ 100ሺ ብር ግምት ያለው ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ፣ጠዋሪ ለሌላቸው አረጋውያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ድጋፍ በማድረግ በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ

በሆሳዕና ከተማ የጤና ስፖርት ማህበር የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ 100ሺ ብር ግምት ያለው ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ፣ጠዋሪ ለሌላቸው አረጋውያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ድጋፍ በማድረግ በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጳጉሜ 03/2014 ዓ.ም

የማህበሩ ስብሳቢ ወጣት ደስታ ገ/ወልድ እንደገለጹት ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከስፖርት እንቅሰቃሴ ባሻገር በማህበራዊ አገልግሎቶች በመሳተፍ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል።

አክለውም ማህበሩ በዛሬው ዕለት 10ኛ ዓመቱን ሲያከብር ከችግኝ ተከላ በተጨማሪ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ሁለት ሙኩት ፍየሎች በስጦታ ያበረከተ ሲሆን ለ15 አረጋዊያን የገንዘብና ለ15 ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ በየነ ሻንቆ ማህበሩ ለመከላከያ ሰራዊትና ለችግር ተጋላጭ ወገኖች ላደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ የጀመሩትን አርአያነት ያለው ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።

የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ታደሰ በበኩላቸው የሰላም ስፖርት ማህበር ከዚህ ቀደም እያከናወነ ያለዉን መልካም ተግባር አጠናክሮ በመቀጠሉ ምስጋናቸውን ገለጸው በቀጣይም በሁሉም ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ መልዕክት በማስተላለፍ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤትም ማህበሩ ጎን መሆኑን ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅናና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል ።

Share this Post