14
Nov
2022
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ህዳር 03/2015 ዓ.ም
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ እንደገለፁት ህፃናት መብታቸዉንና ግዴታቸውን እንዲያዉቁ የህፃናት ፓርላማ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ከስልጠናው ባገኙት ልምድ አቅማቸውን በመገንባት የደህንነትንና ሰብአዊነት ክብር ማስጠበቅ የሚያስችል ስልጠና ነው ብላዋል ።
የስልጠና አስልጣኞች አቶ አበበ አቡረና አቶ ዳዊት አበበ በየበኩላቸው ስልጠናው የህፃናትን ተሳትፎ ለማጎልበትና ለመበረታታት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በህፃናት ላይ የሚፈፀሙትን አስተዳደራዊ በደሎችን ፈጣን ምላሽ ማገኛት የሚችሉበትን አቅም የሚፈጥር ስልጠና ነው ስሉ ገልፀዋል ።
ከአንዳንድ ሰልጣኞች የተሰጠ አስተያየት የህፃናትን መብትና ግዴታቸውን ለማስከበር የሚያስችል፣ የህፃናትን ተሳትፎ ለማጎልበትና ለመበረታታት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል ።