11
Oct
2022
ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ለተመደቡ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብርም ተካሄደዋል።
።።።።።።።።።መስከረም 26/2015 ዓ.ም ።።።።።(ሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለተመደቡ መምህራን፣ ሱፐርቨይዘሮችና ሌሎችም የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር መካሄዱ ተገለፀ።
በመርሃ ግብር ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ እንግዶችን የሰላም አምባሰደር ወደ ሆነው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
ዶ/ር ሀብታሙ አበበ አያይዘውም የፈተና ዓላማ በራስ የመተማመን ዜጋ መፍጠርና የትምህርት ጥረት ማስጠበቅ ሲሆን ለፈተና የተመደባችሁ ሁሉ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ተማሪዎች ተረጋግቶ እንዲፈታኑ ከፍተኛ ሚና አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞች ዛሬ ከመስከረም 26/2015 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቢ መግባት ጀምረዋል። (ዘገባው የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ነው። )