ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ

ጥቅምት 02/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

ላላፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም ተጠናቋል።

ፈተናው በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ የፈተናው ሂደት ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ ምስጋና አቅርበዋል።

ፈተናው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተሰጠበት ዋናው ዓላማ በራስ የሚተማመን ዜጋ መፍጠር እና ብቁ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ገ

ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለውጤታማነቱ ለተጉ፣ ለጣሩ፣ ጊዜአቸውን ለሰጡ እና በቅንጅት ለሠሩ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ ተፈታኝ ተማሪዎች ተግባራዊ በማድረጋቸው ፍፁም ሰላማዊ የፈተና ሂደት እንዲሰፍን ያገዙ መሆኑን ጠቁመው ተፈታኞች ላሳዩት መልካም ስነ-ምግባር ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን መልካም እድል እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የሚመለከተው አካል ከወዲሁ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘው መረጃ ያመልክታል።

Share this Post