በአገራችን ኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ሀገር የማፍረስ ሴራ በመቃወምና መከላከያ ሰራዊታችንን በመደገፍ ''ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምፄን አሰማለሁ'' በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና ከተማ ጥቅምት 12 የፊታችን ቅዳሜ ደማቅ ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

ጥቅምት 10/2/2015ዓ.ም

የሆሳዕና አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ ደ/ር ደበበ ገብሬ ዛሬ እንደገለጹት የሆሳዕና ከተማና አካባቢው ህብረተሰብ የሚሳተፍበት የድጋፍ ሰልፍ በሠላም ለማጠናቀቅ ዝግጅት በማደረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው በዕለቱ በከተማው የሚገኙ ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች እስከ ጠዋቱ አራት ሰዓት የሰልፍ ስነ-ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ተቋሞቻቸውን ዘግተው የሰልፋ ተካፋዮች እንዲሆኑ አሳስበዋል ።

አክለውም በከተማው ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ መነሻውን ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ በማድረግ በአብዮ ኤርሳም ስቴድየም የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ዋና ዓላማ ለአገራችን ሉአላዊነት መከበር አንደ ዜጋ የሚጠበቅብንን ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ከመንግስታችን ጎን መቆማችንን ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

Share this Post