17
Aug
2022
በሆሳዕና ከተማ የሴች ዱና ቀበሌ በመንደር 12 ማህበረሰብ ተሳትፎ 1 ኪ.ሜ በላይ የጠጠር መንገድ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተገለፀ ።
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም
በሆሳዕና ከተማ የሴች ዱና ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ከሣ እንደገለፁት የመንደር 12 ነዋሪዎች የእኛን አካባቢያችንን በእኛ ማልማት እንችላለን በሚል ወኔ ከጠባቂነት የወጣ ማህበረሰብ በመሆኑ የጠጠር መንገድ ማስጀመሪያ ከ150,000 ብር በላይ በመወጣት እየሠሩ መሆናቸውን በመጥቀስ አመሰግነዋል ።
አክለውም ኃላፊዉ ሌሎችም መንደራትም የእንደዚህ ተሞክሮ በመውሰድ ከጠበቂነት በመወጣት በራስ ማልማት እንደሚቻል ጠቁመው ቀበሌው በሚሠሩ መሠረተ ልማቶች የበኩሉን አስተኦጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልፀዋል ።
የመንደሩ የልማት ቡዱን መሪዎች በበኩላቸው በመንደራችን የመንገድ ችግር በመኖሩ የተነሳ መንግስትን ከመጠበቅ እኛ በእኛ የመንገድ ፣ውሃ እና የመብራት ዝርጋታ መሠረተ ልማት ለመሥራት ከአንድ ዓመት በፊት ተቅደው ከነበሩ ተግባራት አንዱን እውን ማድረጋቸውን ጠቅሶ የቀበሌውና የከተማው መንግስት የበኩላቸውን አስተኦጽኦ በማከል ፣ በመመቻቸት ከጎናችን መቆም አለበት ብለዋል ።