በሆሳዕና ከተማ የአራዳ ቀበሌ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2014 ዓ.ም የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ለግንባር ቀደም ሠራተኞች የዕውቅና ሰርተፊኬት አበረከተ ።

የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 06/2014 ዓ.ም

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አድነው ሠዴቦ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት ዓላው ግንባር ቀደም ሠራተኞችን ለማበረታታት ሲሆን በቀበሌው ከዕቅድ በላይ ገቢ እንዲሰባሰብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎችና ተቋማት የዕውቀትና ሰርተፊኬት ሽልማት ተሰጥቷል ።

የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ መሼ በበኩላቸው በቀበሌው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 39 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከዕቅድ በላይ 69 ሚሊየን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን የሐምሌ ወር አፈፃፀም በመገምገም በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል ።

በኘሮግራሙ ላይ የከተማው ም/ከከንቲባ አቶ በየነ ሻንቆ ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊዎች ና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

አንዳንድ ባለሙያዎች በሰጡት አሰተያየት የተሠጣቸው ዕውቅና በቀጣይ ይበልጥ ለመስራት የሚያነሳሳቸው መሆኑን ገልፀዋል።

Share this Post