የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ለ2015ዓ.ም ያሆዴ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ ።

የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳች ጽ/ቤት መስከረም 11/2015 ዓ.ም

የከተማው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ እዮብ እንደገለፁት የዘንድሮው ያሆዴ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በሀድይ ነፈራ በልዩ ዝግጅት ይከበራል።

የከተማችን ጽዳት በመጠበቅ በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የብሔሩ ተወላጆችና አጋሮች ለመቀበል የእንግዳ ማረፊያ ፔንስዮኖችና ሆቴሎች መዘጋጀታቸውንም አቶ አሸናፊ ገልፀዋል ።

በተጨማሪም በዓሉን ለማድመቅና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ለመቀበል የተለያዩ ዝግጅቶች አየተደረጉ ሲሆን በነገው ዕለት በዓሉን በከተማ አስተዳደር ደረጃ እንደሚከበርም ኃላፊው ጠቁመዋል

በመጨረሻም በዓሉ በዩኒስኮ በቅርስነት ለማስመዝገብ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በማሳሰብ እንኳ ለያሆዴ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል ።

Share this Post