23
Sep
2022
የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መስከረም 12/2015 ዓ.ም
በበዓሉ አከባበር መርሀ ግብረ ላይ የብሔሩ ተወላጆች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የአመራር አካላት ፣ መንግስት ሠራተኞች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የኢን/ኢ/ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ሸንቆ በዓሉን አአስመልክቶ የዘንድሮው "ያሆዴ" የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ሲበበር ዘርፈ ብዙ እሴቶች መካከል ሥራ ወዳድነት፣ መከባበር ፣ መጠያየቅ ፣ ፍቅር ፣ ተሳታፊነት ሌሎችም በረካታ ወግና ባህል ቋንቋ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል ።
አክለውም ኃላፊው በዓሉ በዩኒስኮ በቅርስነት ለማስመዝገብ ዘርፍ ብዙ ሥራዎች እየተሠራ ያለው መሆኑን በማሳሰብ በሀገርና በውጭ የሚገኙ የሀዲያ ተወላጆችና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳ "ለያሆዴ"የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በሠላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውንም ገልጸዋል ።
የከተማው ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ እዮብ በበኩላቸው "ያሆዴ"የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል በየዓመቱ መስከረም አጋማሽ ሲከበር በብሩህ ተስፋ ፍቅር ፣ የሬድኤት ፣ የሰላምና የበረከት ተምሳሌት መሆኑን ትርክት ነዉ ስሉ ተናግረዋል ።