በሆሳዕና ከተማ ታምራት ደበሮና ቤተሰብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከ27 ሚልዮን በላይ የተሠራ የዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 15/2014 ዓ.ም
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የፌዴራል ፣ የክልል፣የዞን፣ከተማና ቀበሌያት አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል ።
የዕለቱን የምረቃ ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም መጫና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ በየነ ሸንቆ በየበኩላቸው የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ዕድገትን በመፋጠን በቴክኖሎጂ የተገነባ ትውለድ ለመፍጠር የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሠራ ያለው መሆኑን ጠቁመው በተመሳሳይ መልኩ መንግስት ባመቻቸው መሠረት ግብርና፣ፋይናንስንና የሰው ኃይልን በመጠቀም ዘርፍ ብዙ ተግባራት ላይ በማህበር በመደራጀት ሥራ ጠበቅ ሰይሆን ፈጣሪ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል ።
ታምራት ደበሮና ቤተሰብ ኃላነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የዱቄት ፋብሪካ ባለቤትና ሥራ-አስኪያጅ አቶ ታምራት ደበሮ ባስተላለፉት መልዕክት ለሥራ ምቹ ሁኔታዎችን ያመቻቸው መንግስትን ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ እንዲሁም የሆሳዕና ቅርንጫፍ ልማት ባንኩንና ሌሎችንም ተቋማትንና ግለሰቦችን አመሰግነዋል ።
አክለውም ሥራ-አስኪያጁ ፋብሪካው ከ27 ሚልዮን በላይ የተገነባ ስሆን በቀን 420 ኩንታል የመፍጨት አቅም ያለው ዘመናዊ የዱቄት ፋብሪካ መሆኑን በባለሙያ የተረጋገጠ እንደሆነና ለ15 ቆምና ለ25 ጊዜያዊ ሠራተኞች ሥራ ዕድል የፈጠራ ነዉ ስሉ ገልፀዋል ።