በሆሳዕና ከተማ የሄጦ ቀበሌ አስተዳደር "ከእኛው ለእኛ "በሚል መሪ ቃል ከቀበሌ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ለ42 አቅመ ደካማ አረጋውያንና ለዘማች ቤተሰቦች የምግብ ፣ የትምህርት ቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም 4/2014 ዓ.ም
የሄጦ ቀበሌ ዋና አስተዳደሪ አቶ ለምቦሮ ሱሎሬና የቀበሌው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ አቦሴ በየበኩላቸው አቅመ ደካማ አረጋዊያንና ለዘማች ቤተሰቦች የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የተደረገው ድጋፍ የምግብ ዱቄት ፣ ዘይት ፣ አልባሳት ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ደብተር ና እስክርቢቶ ከ50 ሽህ ብር ባለይ ግምት እንዳለው ተናግረዋል ።
አክለውም የተደረገው ድጋፍ የመረዳዳት ባህላችን ውጤት መሆኑን ጠቅሰው የሚበላውን በማጣት የሚያድር ወገን እንዳይኖር ሁለም ማህበረሰብ የበኩሉን አስተኦጽኦ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል ።
የሆሳዕና ከተማው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በርከት ታደሰ እንደስተላፋት ለተረጂዎቹ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ስራዎች በመሳተፍ በዘላቂነት ራሳቸውን ለማቋቋም መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።
በመጨረሻም ተረጂዎች በሰጡት አስተያየት የምግብ፣ የአልባሳት ፣የትምህርት ቁሳቁሶች አልባሳት ድጋፍ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።