19
Sep
2022
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም 9/2015 ዓ.ም የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት እንደገለፁት የሀገራችን ሎአላዊነትን ለማስጠበቅ ልጆቻቸውን በመዝመት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ ለዘማች ቤተሰቦቻቸው የተለያዩ አልባሳት ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል ። አክለውም የተደረገው ድጋፍ የመረዳዳት ባህላችን መሆኑን በመገንዘብ የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤቱ ከዚህ በፊትም በተለያዩ ጊዜያት የከተማውን ማህበረሰብን በማስተባበር የተለያዩ ድጋፎችን እየበረከተ የቆየ መሆኑን ጠቁመው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ስራዎች በመሳተፍ ራሳቸውን ለማቋቋም መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ። በመጨረሻም የዘማች ቤተሰቦቻቸው የሰጡት አስተያየት የአልባሳት ድጋፍ ለተደረገላቸው ምስጋና አቅርበዋል ።