ኮሌጁ ድጋፉን በሆሳዕና ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን በፍቅርና ርህራሄ ህብረት ለታቀፉ ህጻናት ነው ያደረገው።
ኮሌጁ በአካባቢው በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች በመሳተፍ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንጀሚገኝ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደሰ ማቲዎስ ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለትም ከ65 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተገዙ 50 ደርዘን ደብተር 50 የመማሪያ ቦርሳና እስኪብርቶና አርሳስ ድጋፍ ለሚሹ 50 ተማሪዎች አበርክቷል።
ድጋፉ ቀጣይነት ያለው መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደሰ በቀጣይም ሌሌች ድጋፍ ለሚያሻቸው ወገኖችን መደገፍ ጨምሮ በሌሎች ማህበራዊ መስኮች ሁሉ በመሳተፍ ለበኩን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በሀዲያ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርና ስልጠና መምሪያ የተቋማት አቅም ግምባታ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ
አቶ ተክሉ ፊታሞ ኮሌጁ ከማህበራዊ ኃላፊነት አንጻር በአካባቢው እያደረገው ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በቀጣይ ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በማሳሰብ ሌሌች በየአካባቢው የሚገኙ ኮሌጆችም ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የሚያከናውናቸውን ማህበራዊ አገልግሎቶች አጉልተው ሊተገብሩ ይገባል ብለዋል።
የደቡብ ሸዋ ቀጠና አጠቃላይ ቤተክርስቲያናት መሪ አቶ ዮናስ ዱባለ በትውልድ ላይ የሚሰራ ስራ ሀገር ላይ የሚሰራ ስራ ነው ቤተክርስቲያኒቱ በትውልድ ላይ እየሰራች ያለውን ስራ ለደገፈው አትላስ ኮሌጅ ምስጋና አቅርበዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ህጻናት የተደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ትምርህታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ የሚያግዝ በመሆኑ ኮሌጁን አመስግነዋል።
ኮሌጁ ለ50 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው 1ደርዘን ደብተር 1 ቦርሳና ኢስኪብርቶና እርሳስ ነው ድጋፍ ያደረገው።