18
Nov
2022
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ህዳር 9/2015ዓ.ም
በከተማው ዋና ዋና መንገዶች ላይ በተካሄደው ጽዳት ዘመቻው ላይ የወጣት አደረጃጀቶችና የአመራር አካላት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።
የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ ሊሬ ጀማል እንደገለጹት የከተማው የፅዳት ችግር የሚፈታው እኛው እንጂ ሌላ አካል አለመሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ንጽሕና በማጠናከር ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የፅዳት ዘመቻው በሁሉም ቀበሌ አስተዳደሮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል ።